Ethiopian Women in Water Association (EWIWA)
Open Hours
Our Association
EWIWAr Office
Region: Addis Ababa,
City: Addis Ababa
Bole Woreda 04
የኢትዮጵያ ሴቶች የውሃ ማህበር በታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም 2ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በውሃና ኢነርጂ ሚ/ር መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄደ ስሆን፣ የማህበሩ ነባራዊ ሁኔታና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ የዉይይቱ ቁልፍ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡
በዕለቱም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አዳነች ያሬድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ሲያስተላልፉ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች የዉሃ ማህበር የተቋቋመው በዋነኛነት በዉሃ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት በዘርፋ የተሰማሩ ሴቶችን ለማብቃት፣ የልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበትን የግንኙነት መረቦች ለመፍጠር እና በአመራርና በባለሙያ ደረጃ በዉሃ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ እንድያድግ አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዉ፣ ስለተደረገዉ ቀና ትብብር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋን በማህበሩ ስም አመስግነዋል፡፡
የውይይቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለፁት እንደሀገር በሰፊው የታለመውን የልማት ስራዎችን ማሳካት የምቻለዉ ሴቶችን በአግባቡ ማሳተፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን ገልፀው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለዉ ድህነትና ኋላ ቀርነት ገፈት ቀማሽ የሆኑ ሴት እህቶቻችንን ለመርዳት፣ ማህበሩ ጠንክሮ መስራት እና ለሌሎችም አርአያ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለዉም ማህበሩ የበለጠ እንድጠናከር አቅም በፈቀደ ሁሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንደምደግፈዉ ገልፀዋል፡፡ በዉሃ ዘርፍ የሥርዓተ-ፆታ ማካተቻ (የጀንደር ሜንስትሪሚንግ) የአቅም ግንባታ ስልጠና የተሰጠ ስሆን በበጀት አመቱ እቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ፣ አባላቱ ከእቅዱ ውስጥ የራሳቸዉን ድርሻ በመዉሰድ አስተዋፅኦ እንድያደርጉ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባኤዉ ተጠናቋል፡፡