News

3ኛዉ የኢትዮጵያ ሴቶች የዉሃ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ እና አንደኛ አመታዊ ኮንፍረንስ ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ LION OF JUDAH JESUS INTERNATIONAL HOTEL መካሄድ ተጀምሯል ።

በጠዋቱ የስብሰባ ክ/ጊዜ በዶ/ር መሰረት ዳዊት፣ በዶክተር ቀናቱ አንጋሳ፣ በዶክተር አዳነች ያሬድ እና በወ/ሮ ሜቲናፍ  ደረጀ ስለ ህብረቱ ቀጣይ እቅድ እና የተሰሩ ስራዎች ገለፃ ተደርጓል። በስብሰባው ላይ በህብረቱ የተዘጋጀ አጭር ቪዲዮ የተላለፈ ሲሆን በቪዲዮ የማህበሩ አመሰራረት እና የማህበሩ መሪዎች እና  አባላት እንዴት ወደ ማህበሩ እንደተቀላቀሉ እንዲሁም ባላቸው እውቀት እና ልምድ ማህበሩን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል ።

ከሰአት በኋላ ባለው ፕሮግራምም በማህበሩ መስራች እና ፕሬዚዳንት በዶክተር አዳነች ያሬድ የወደፊት እቅዶች ገለፃ ተደርጓል። እሱን ተከትሎ እስካሁን ባለው የህብረቱ ጉዞ የታዩ ድክመቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በማህበሩ አባላትም በተለያዩ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎ ሀሳቦች ፀድቀዋል። በመጨረሻም በአንድም በሌላ መንገድ ያልተከናወኑ እቅዶች በሚቀጥለው ያለመሰናክል መከወን እንደሚቻል ውይይት ተደርጓል ።