News

የኢትዮጵያ ሴቶች የውሃ ማህበር የመጀርያውን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ::

ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዚያ 24/2015 እና 26/2015 የኢትዮጵያ ሴቶች የውሃ ማህበር አባላት በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስተር መ/ቤት ዉስጥ ባለዉ በኢትዮጵያ ሴቶች የውሃ ማህበር ቢሮ ስብሰባ አካሂደዋል፡፡

በስብሰባው የማህበሩ መስራች በሆኑት በዶ/ር አዳነች ያሬድ በኩል ለእለቱ ውይይት የተያዙ አጀንዳዎች ዙሪያ ለአባላቱ ገለፃ ተደርጓል፡፡

በቀጣይ ስለ ማህበሩ አላማና ለማህበሩ ቀጣይ እቅድ በዋነኝነት የማህበሩን አባላት እንዴት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ማብቃት እና አሁን ካሉት ደረጃ ከፍ ማድረግ ይቻላል? በሚለው ዙሪያ ላራ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከአባላቱ መካከል የእርስ በእርስ ትውውቅ የተደረገ ሲሆን ማህበሩን በቀጣይ እንዴት ለኢትዮጵያ ሴቶች የተለያዩ ማህበራዊ ገፆችን በመጠቀምም ሆነ ከአባል በመገናኘት በሰፊውና በፊጥነት የበለጠ ቅርብ ማድረግ ይቻላል በሚለው ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡

 

 

በመቀጠልም ከማህበሩ ቀጣይ እቅድ በመነሳት እያንዳንዱ አባል የተያዙ እቅዶች መሬት ለማስነካት በግሉ የሚከናወን የስራ ሀላፊት ተቀብሏል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የተገኙ አባላት ባላቸው እውቀት እና ጊዜ ማህበሩን ለመርዳት ቃል ገብተዋል፡፡